Catch the upcoming 2025/26 Football Season on DStv!  - DStv Ethiopia

ተወዳጆቹ የአውሮፓ ሊግ ውድድሮች ዳግም ሊጀምሩ ቀናት ቀርተዋል

News 13 July 2025

የእግር ኳስ ውድድሮች ሁሉ መገኛ የሆነው ዲኤስቲቪ የ2025/26 እግር ኳስ ውድድሮች ከነሀሴ ጀምሮ ማስተላለፍ እንደሚጀምር አስታውቋል።

ተወዳጆቹ የአውሮፓ ሊግ ውድድሮች ዳግም ሊጀምሩ ቀናት ቀርተዋል

የአውሮፓ እግር ኳስ ሊግ ውድድሮች ዳግም ሊጀመሩ ጥቂት ቀናት የቀሩ ሲሆን ዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ደግሞ ሁሉንም ውድድሮች ይዞላችሁ ይቀርባል። ውብ እግር ኳስ ውድድሮችን በማስተላለፍ የሚታወቀው ሱፐርስፖርት ደግሞ ከመቼውም ጊዜ በላይ በሙሉ አቅሙ ከብዙ አማራጮች ጋር ለተመልካቾች ሊያቀርብ ዝግጅቱን አጠናቋል።  

የእግር ኳስ ውድድሮች ሁሉ መገኛ የሆነው ዲኤስቲቪ 2025/26 እግር ኳስ ውድድሮች ከነሀሴ ጀምሮ ማስተላለፍ እንደሚጀምር አስታውቋል። ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ፣ የስፔን ላሊጋ እና የጣልያን ሴሪ ውድድሮች በተለያዩ አማራጮች ሱፐርስፖርት ይዤ መጥቻለሁ ብሏል። 

የአምናው እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ሊቨርፑል እግር ኳስ ክለብ አሸናፊነቱን ለማስጠበቅ የሚያደርጋቸው ፍልሚያዎች፣ ኢንተርሚላንን በአንድ ነጥብ በመብለጥ የሴሪኤው አሸናፊ የሆነው ናፖሊ እንዲሁም የላሊጋውባለድል ባርሴሎና የአምናውን አሸናፊነታቸውን ለማስቀጠል ዘንድሮም ይጠበቃሉ። ሱፐርስፖርት ከአውሮፓ ሊጎች ውድድሮች ባለፈ በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ፣ ዩሮፓ ሊግ እና ተወዳጅ የሆኑ እንደ ኤፍኤ ካፕ መሰል ውድድሮችን ማስተላለፉን እንደሚቀጥልም አስታውቋል።  

380 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን እንደሚያስተላልፍ የገለጸው ሱፐር ስፖርት ለዚህም ጨዋታዎቹን በዲኤስቲቪ ቻናል 223 እንደሚያስተላልፍም ገልጿል። እንዲሁም በሱፐር ስፖርት ቻናል 224 ደግሞ 300 የስፔን ላሊጋ ጨዋታዎችን አስተላልፋለሁም ብሏል። የዲኤስቲቪ ፕሪሚየም ደንበኞች ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድሮችን ጨምሮ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ፣ ላሊጋ፣ ሴሪ ኤ፣ ኢሮፓ ሊግ፣ ኤፍኤ ካፕ እና ሌሎች ስፖርታዊ ውድድሮችን በሱፐርስፖርት ፉትቦል ኤችዲ፣ ሱፐር ስፖርት ላሊጋ፣ ሱፐር ስፖርት ፕላስ እና ሱፐር ስፖርት ቫራይቲ ይተላለፋሉ።  

ለዲኤስቲቪ ሜዳስፖርት ደንበኞች ደግሞ ከአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ውስጥ 125 ውድድሮችን የመመልከት እድል ተመቻችቶላቸዋል ተብሏል። እንዲሁም የዲኤስቲቪ ሜዳ ደንበኞች 300 በላይ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ፣ ኤፍ ኤካፕ እና ካራባኦ ካፕ ውድድሮች ቀርቦላቸዋል። የዲኤስቲቪ ቤተሰብ እና ጎጆ ደንበኞች የተመረጡ ቻምፒዮንስ ሊግ፣ ፕሪሚየር ሊግ፣ ላሊጋ እና ሴሪ የቀጥታ እግር ኳስ ውድድሮችን በሱፐር ስፖርት ፉትቦል ቻናል ላይ እንደሚያገኙ ተገልጿል።  

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከመጀመሩ በፊት የሚደረገው የማህበረሰብ ወይም ኮምኒቲ ሽልድ ዋንጫ ነሀሴ 4 ቀን 2017 . በፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ ሊቨርፑል እና ኤፍኤካፕ አሸናፊው ክሪስታል ፓላስ መካከል ይካሄዳል። አርብ ነሀሴ 9 ቀን 2017 .  ደግሞ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ይጀመራል። እንዲሁም ነሀሴ 10 እና 11 ቀን 2017 . የሚካሄደው የስፔን ላሊግ መክፈቻ ጨዋታ በባርሴሎና ርካ መካከል ይካሄዳል። ነሀሴ 17 ቀን 2017 . የሚጀምረው ጣልያን ሴሪ ደግሞ የአምናው አሸናፊ ናፖሊ ከሳሱሎ ጋር ይጫወታል። 

Back to News