ፈጣኑንና ገደብ አልባውን የዲኤስቲቪ ስትሪም ይቀላቀሉ
ዲኤስቲቪ ስትሪም ዲኮደርና ዲሽ ሳያስፈልግዎት መጠቀም የሚችሉት ራሱን የቻለ የዲኤስቲቪ ይዘቶችን የሚያገኙበት የበይነ መረብ ፕላትፎርም ነው።

ለደንበኞች ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎቶችን ለማቅረብ ከምናደርጋቸው ጥረቶች መካከል ዘመኑን የዋጁ አማራጮችን ማዘጋጀት አንዱ ነው። ዲኤስቲቪ ስትሪም ደግሞ የዚህ ማሳያ ነው።
ዲኤስቲቪ ስትሪም ዲኮደርና ዲሽ ሳያስፈልግዎት መጠቀም የሚችሉት ራሱን የቻለ የዲኤስቲቪ ይዘቶችን በዲኤስቲቪ ስትሪም መተግበሪያ በኩል የሚያገኙበት የበይነ መረብ (ኢንተርኔት) ፕላትፎርም ነው።
በዲኤስቲቪ ስትሪም አገልግሎት በቀጥታ ስርጭትም ሆነ ያለ ቀጥታ ስርጭት የሚተላለፉ ሀገርኛና ዓለም አቀፍ የስፖርትና መዝናኛ ይዘቶችን በፈለጉት ዲጂታል ዲቫይስ ( በሞባይል ስልክዎ፣ በቴሌቪዥንዎ፣ በታብሌትዎ አለያም በላፕቶፕዎ) በመጠቀም በዲኤስቲቪ ስትሪም መተግበሪያ በኩል በጥራት ማግኘት ያስችልዎታል።
በዲኤስቲቪ ስትሪም በመደበኛው የዲኤስቲቪ የሳተላይት ስርጭት የሚያገኟቸውን ይዘቶች ማለትም ፊልሞችን፣ ሾዎችን፣ የስፖርት ፕሮግራሞችንና ሌሎችንም መመልከት ይችላሉ። ዲኤስቲቪ ስትሪም በፈለጉት ሰዓት፣ በፈለጉት ቦታና በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆነው መመልከት የሚችሉት በመሆኑ ተመራጭና ተወዳጅ እየሆነ የመጣ የስትሪሚንግ አገልግሎት ነው።
ዲኤስቲቪ ስትሪምን በተለያዩ የዲኤስቲቪ ፓኬጆች ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ራሱን ችሎ ደንበኛ መሆን የሚችሉት የአገልግሎት አማራጭም ነው። በመሆኑም ከጎጆ ፓኬጅ ጀምሮ ከቤተሰብ፣ ከሜዳ፣ ከሜዳፕላስ እና ከፕሪሚየም ፓኬጆች በመረጡት ፓኬጅ ደንበኛ ሆነው ተወዳጅ የሀገር ውስጥና ዓለምአቀፍ የስፖርትና መዝናኛ ይዘቶችን መኮምኮም ይችላሉ። የዲኤስቲቪ ስትሪም ተጠቃሚ ለመሆን ደግሞ ቀላል ነው። ወደ ድረገጻችን ገብተው www.dstv.com ከላይ የሚያገኙት ቶፕ ባነር ላይ "dstvstream" የሚለውን ይምረጡ፣ ከሚመጣሎት ዝርዝር ውስጥ የሚፈልጉትን ፓኬጅ ይምረጡ ፣ በመጨረሻም የዲኤስቲቪ ስትሪም አካውንት ይመዝገቡና ክፍያ ይፈፀሙ። አለቀ! ይህን ያህል ቀላል ነው።
በዲኤስቲቪ ስትሪም እስከ 10 የሚደርሱ የሚጠቀሙባቸውን ዲቫይሶች ማስመዝገብ ይችላሉ። ከነዚህ እየመረጡ በተመሳሳይ ጊዜ ሁለት ዲቫይሶች ላይ መመልከት ይችላሉ።
ለበለጠ መረጃ FAQ ይጎብኙ።