ሪሞትዎን ያንሱ ፤ ዲኮደርዎንም ያስሱ - የአፍሪካን ወር በዲኤስቲቪ ይቃመሱ!

News 14 May 2024

መልካም የአፍሪካ ወር - ከአፍሪካ ታሪክ ነጋሪው ዲኤስቲቪ ጋር ይሁንልዎ!

ሪሞትዎን ያንሱ ፤ ዲኮደርዎንም ያስሱ - የአፍሪካን ወር በዲኤስቲቪ ይቃመሱ!

መልቲቾይስ በዚህ የአፍሪካ ወር ዲኤስቲቪ ሁሉም ደንበኞች ዲኮዲራቸውን አብርተው የአፍሪካን ታሪክ ነጋሪውንና የመዝናኛውን ዓለም ዲኤስቲቪን እንዲመለከቱ ጥሪ ያቀርባል። ደንበኞች፤ በዚህ ግንቦት ወር ምቹ በሆነው MyDStv መተግበሪያ ጥቅላቸውን ገዝተው የአፍሪካውያንን ተሰጥኦ፣ ባህል እና ፈጠራ ትኩረት የሚሰጡ ሰፊ የትዕይንት ምርጫዎችን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ።

በሜዳ (ኮምፓክት) ፓኬጅ የሚገኘውን የዛምቢያን ልብ አንጠልጣይ ድራማ “ዙባ” ምዕራፍ 8 ቢመለክቱ በአፍሪካዊቷ ዛምቢያ የ “ዛምቤዚ ማጂክ” ቻነል የ “ሶሳላ እና የጄሬ ቤተሰቦች” ሚስጥሮችን በአፍሪካዊ የሲኒማ አቀራረብ ይመለከታሉ፡፡

ከኢትዮጵያ ደግሞ አዲሱና በአጭር ጊዜ አነጋጋሪ የሆነውን “የረቂቅ መንገድ”ን ጨምሮ “ሃምዛ” እና “አፋፍ” ን ከሌሎች መሳጭ ይዘቶች ጋር ይመለከታሉ፡፡ በአቦል ቻነል እየተላለፈ የሚገኘው ልብ አንጠልጣዩ “የረቂቅ መንገድ” ከክፍለ ሀገር ለስራ ወደ አዲስ አበባ የመጣችዉን “ረቂቅ” ውጣ-ውረድ ልብ እያንጠለጠለ ይተርካል፡፡ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ምሽት ከ2፡30 ሰዓት ጀምሮ በአቦል ቻነል በጎጆ ፓኬጅ እየተላለፈ ይገኛል፡፡

ዲኤስቲቪ እርስዎ ቤትዎ ቁጭ ብለው ወደ አንጎላም ይዞዎት ይጓዛል፤ በ “Kwenda Magic” ላይ በ “ቤተሰብ” ፓኬጅ እየቀረበ የሚገኘውን የአንጎላውን ተወዳጅ “ኦ ካካ ታልንቶስ” የወጣት ዳንሰኞችን ማራኪ ዓለም ያስመለክትዎታል፡፡

በዚህም አያበቃም፡፡ ወደ አፍሪካ ታላቋ ሀገር ደቡብ አፍሪካም በሃሳብ ሰረገላ ያንሸራሽርዎታል፡፡ በ “ትምህርት ቤት” ትስስር ጉዳዮች ላይ ያጠነጠነውና በኤም-ኔት “ፕሪሚየም ፓኬጅ” በልዩ ጥራት የተዘጋጀውን ባለ አራት ክፍል ዘጋቢ ፊልም ይኮመኩማሉ፡፡ ዶክመንተሪው በዋናነት በደቡብ አፍሪካ የወንዶች ትምህርት ቤቶች ውስጥ የተደረገውን ድብቅ ጥቃት ያሳያል። ይህን ዶክመንተሪ ሐሙስ ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ.ም ምሽት 4፡00 ሰዓት ይጀምራል።

የስፖርት አድናቂዎች ደግሞ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመንን ማብቂያ ይመለከታሉ፡፡ የሊቨርፑሉን አጥቂ የግብጻዊውን የመሃመድ ሳላህን የጎል ማስቆጠር ችሎታን ብሎም በአርሰናልና ማንቸስተር ሲቲ መካከል የሚደረገውን የዋንጫ ትንቅንቅ በሱፐርስፖርት ቻናሎች በልዩ ጥራት መመልከት ይችላሉ፡፡ በአፍሪካ ወር በእንግሊዝ የደመቁትን አፍሪካውያን ተጨዋቾችም ያስታውሳሉ፡፡

ሁሌም እንደሚደረገው ዘጋቢ ፊልሞች በልዩ ጥራት ተሰንደዋል፡፡ ለተፈጥሮ ጉዳዮች ቀናኢ ለሆኑ የዲኤስቲቪ ተከታታዮች አፍሪካዊውን የ “ሻርክ ሳፋሪ” በ `Discovery Channel` እና `Wild Botswana on Nat Geo Wild” በቤተሰብ ፓኬጅ ላይ መመልከት ይችላሉ፡፡ በእነዚህ የተፈጥሮ ጉዳይ ዶክመንተሪዎች የአፍሪካን የበለፀገ ብዝሃ ህይወት እንዲያስሱ ዲኤስቲቪ በአክብሮት ይጋብዛል። እሑድ ግንቦት 11 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 6፡10 ሰዓት እና ምሽት 1፡45 ሰዓት ሪሞትዎን ከዲኮደርዎ ያገናኙ - እነዚህ ውብ ዘጋቢ ፊልሞች አያምልጡዎ።

በዚህ የአፍሪካ ወር፣ ከዲኤስቲቪ ጋር የበለጠ ይቅረቡ፣ ይገናኙ፡፡ የአህጉሪቱን የበለጸገ ታሪክና ወግ በቤትዎ ሆነው ይመልከቱ።

ምናልባት ከሌለዎት የMyDStv መተግበሪያን ያውርዱ፡፡ ለእርስዎና ለቤተሰብዎ መዝናኛ ምርጫዎችዎ የበለጠ የሚስማማውን ጥቅል ይምረጡ። አንድ ወር የሚፈጀውን የአፍሪካ ወር ደማቅ አከባበር በአፍሪካዊ ባህል ይቀላቀሉ፤ የአፍሪካውያንን የጥበብ ትሩፋት እየኮመኮሙ ወሩን ያክብሩ!

መልካም የአፍሪካ ወር - ከአፍሪካ ታሪክ ነጋሪው ዲኤስቲቪ ጋር ይሁንልዎ!

Back to News